If the information on this translated website is unclear, please contact us at 360.902.3900 for help in your language of choice.

የባለሙያ እና የንግድ ፈቃድ አገልግሎት መቋረጥ

የዘመነው 5 p.m. April 13, 2022

ሙያዊ ፍቃድ ኣሰጣጥ ሥርዓት በድጋሜ ጀምሩዋል

ከ መጋቢት 1 ቀን 2022 ዓ.ም. ጀምሮ የሙያ Department of Licensing (DOL) በድጋሜ መስራት ጀምሩዋል ከዚ በኋላ ደንበኞች ለማደስ ፍላጎታቸውን ለፈቃድ መስጫ ክፍል ማመልከት ኣይጠበቅብቸውም ግለሰቦች የሙያ ፈቃዳቸውን ማደስ እና አዲስ የሙያ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት በኢንተርኔት ይችላሉ።

DOL የባለሙያ ፈቃድ ኣሰጣጥ የመረጃ ማዕከልን በተመለከተ ኣጠራጣሪ ድርጊቶችን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ደርሶት ስለንበር፤ የደንበኞቻችንን መረጃ ደህንነትን ለማስጠበቅ ከጥር 24 ቀን 2022 ዓ.ም. ጀምሮ DOL ፖርታሉን ከመስመር ውጪ ኣድርጎታል።

DOL ፖርተሩን ወደ ስራ አገልግሎት ከመመለሱ በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው የኢንተርኔት ደህንነት ባለሙያ፣ በማስተናገድ ሥራ ላይ በተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም በዋሽንግተን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ (Washington Technology Solutions, WaTech) በመታገዝ ጥልቅ ምርመራ አካሂዷ ሕግ አስከባሪዎችም ስለዚህ ጉዳይ ያቃሉ። በአሁኑ ጊዜ የሙያ ፈቃድ ሰጪው ክፍል አስተማማኝ ሁኔታ እየሠራ እንደሆነ እንዲሁም በቅርበት መከታተላቸውን እንደምንቀጥል እርግጠኞች ነን።

የአሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪዎች ፍቃድ ስርዓትን ጨምሮ በ DOL በሚሰራ ማንኛውም ስርዓት ላይ ሌላ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ አልተገኘም፤ሁሉም በቅርበት ክትትል ላይ ናቸው። የትኛውየሥርዓቱ ክፍል እንደተጣሰ እና እንዴት እንደተጣሰ መመራመራችንን እንደቀጠልን ነው ። ተጨማሪ መርጃ ስናገኝ እናሳውቃችዋለን።

በፍቃድ ሰጪ ፖርታል ውስጥ ያለው አንዱ አማራጭ፣ በ Pay by Employer በመባል የሚታወቀው፣ ሥራ ላይ አልዋለም። ይህንን አማራጭ ጥቂት ሙያዎች ነው ሚጠቀሙት ለምሳሌ የጥበቃ ሰራተኞች። ፈቃዳቸውን ለማሳደስ ሚፍልጉ ግለሰቦች ያላቸውን ሙያዊ ፕሮግራም ያነጋግሩ

ኣገልግሎቱ በተቋርጠ ግዜ ጊዜው ያለፈባቸው ባለፈቃዶች ላይ ያለውን ተጽእኖ ለመገደብ DOL እስከ ሚያዝያ 1, 2022 ድረስ ሁሉንም የዘገየ ቅጣት ወዲያውኑ እያስወገደ ነው።

ማሳወቂያ ደብዳቤዎች እየተላኩ ነው።

የDOL ምርመራ በእርስዎ የDOL ፕሮፌሽናል ወይም የንግድ ፍቃድ መዝገብ ውስጥ ያለው የግል መረጃ ባልተፈቀደለት ሰው ሊገኝ እንደሚችል አአውቀናል። በያዙት የፈቃድ አይነት ላይ በመመስረት የተጎዳው መረጃ የእርስዎን ስም፣ የኢሜል አድራሻ፣ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር፣ የትውልድ ቀን እና/ወይም የመንጃ ፍቃድ ቁጥርን ሊያካትት ይችላል።

በአደራ የተሰጡን የግል መረጃ ፍቃድ መስጫዎችን ደህንነት በቁም ነገር እንወስዳለን። ድርጅቱ የካቲት 25, 2022 ላይ እክል ለደረሰባቸው ሰዎች የማሳወቂያ ደብዳቤዎችን መላክ ጀመረ። ደብዳቤዎቹ እንዴት ነፃ ክሬዲት ቁጥጥር ማግኘት እንደሚቻል በተመለከተ ዝርዝር መመሪያዎችን ይዘዋል ። እባክዎትን የጊዜ ገደቡን በጥንቃቄ ይመልከቱ፤ግዜው ካለፈ በኋላ በነፃ ክሬዲት ሞኒተር መመዝገብ አይችሉም። የግዜ ገደቡ ሚያዝያ 24, 2022 ነው።

ለ ክሬዲት ጥያቄዎች የጥሪ ማዕከሉ ስልኮች ክፍት ናቸው።

DOL ከሚያቀርበው ነፃ ክሬዲት ቁጥጥር ጋር አብርው ለሚነሱ ጥያቄዎች ድጋፍ ይሰጣል።

ስለ ነፃ ክሬዲት ክትትል ላሉ ጥያቄዎች

  • ስልክ ቁጥር: 360.664.1497
  • የስራ ሰዓት: ከሰኞ እስከ አርብ 9 a.m. – 4 p.m. የፓስፊክ መደበኛ ሰዓት።

የተቀየረው ምንድን ነው?

መንደርደሪያ

የፍቃድ መስጫ መምሪያ (DOL) የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ መንጃ ፍቃዶችን አይሰጥም። መምሪያው በተጨማሪም የውበት ባለሙያዎችን፣ የሪልስቴት ደላሎችን፣ ዋስትና ሰጪዎች/ያዦችን፣ አርኪቴክቶች እና የአሽከርካሪ ስልጠና ትምህርት ቤት አስተማሪዎችን ጨምሮ ለ 39 የንግድ ሥራ እና የሙያ አይነቶች ፍቃዶችን ይሰጣል።

DOL የሙያ እና ሥራ ፍቃድ ወሳጆች መረጃዎችን የሙያ የኦንላይን የፍርድ እና የቁጥጥር መረጃ ስርዓት (Professional Online Licensing and Regulatory Information System, POLARIS) ተብሎ በሚጠራው ሲስተሙ ላይ ያስቀምጣል። ስራዓቱን የበለጠ ተለይቶ በሚታወቅበት ስሙ “የሙያ እና ንግድ ሥራ ፍቃድ መስጫ ስርዓት” ለይታችሁ ልታውቁት ትችላችሁ። ለ23 የተለያዩ አይነት ሙያዎች ስርዓቱ የፍቃድ ማመልከቻዎችን ያሰናዳል፣ ይሰጣል እንዲሁም ያድሳል፤ በፍቃድ ወሳጆች ላይ ከማህበረሰቡ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ይቀበላል እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን ይሰጣል። የሙያ ፍቃድ መስጫ ስርዓቱ ፍቃድ ወሳጆች የወሰዱት ፍቃድ የሚገኝበትን ደረጃ እና ማሟላት የሚያስፈልጓቸውን የትኛውንም መስፈርቶች እንዲቆጣጠሩ ይረዳቸዋል። ስርዓቱ በተጨማሪም ፍቃድ ሰጪ ሠራተኞችን ደንበኞችን በሁሉም ፍቃድ የመውሰድ ፍላጎቶቻቸው ላይ እንዲረዷቸው ያስችላቸዋል እንዲሁም ማህበረሰቡን የአንድን ሰው ፍቃድ የሚገኝበትን ደረጃ እንዲያይ ያስችለዋል።

ምን ተፈጠረ?

በጃኑዋሪ 24 ፣ 2022 በነበረው ሳምንት ውስጥ DOL በሙያ እና ንግድ ሥራ ፍቃድ መስጫ ስርዓት ላይ የሙያ እና የሥራ ፍቃድ መረጃን (ውሂብን) ያካተተ አጠራጣሪ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አወቀ። DOL ወዲያውኑ ሲስተሙን በመዝጋት በ Washington ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ (WaTech) እና በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በአገር አቀፍ ደረጃ በታወቁ ሙያተኞች እገዛ እየተደረገለት ምርመራውን ማካሄድ ጀመረ። ከዚህ በተጨማሪም፣ DOL በሳይበር ደህንነት እና የክስተት ምላሽ በአገር አቀፍ ደረጃ የታወቁ ሙያተኞችን አገልግሎቶች ተጠቅሟል። ለህግ አስፈጻሚም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ደንበኞች የባለሙያ ፈቃድ ለማመልከትና ለማደስ የሚችሉበት የሥርዓቱ ክፍል መጋቢት 1, 2022 ወደ አግልግሎት ተመልሷል ። ጥልቅ የደኅንነት ምርመራ እንዳረጋገጠው ይህ ክፍል የክፍተቱ አካል አልነበረም፤ እንዲሁም በድጋሜ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ያልተፈቀዱ መረጃዎችን እንደማያጋልጥ እርግጠኞች ነን።

በDOL ላይ ያልተፈቀደ የውሂብ መዳረሻ ነበረ?

አዎ። በምርመራችን ላይ ተመስርቶ DOL የሙያ እና ንግድ ፍቃድ መስጫ ስርዓቱ ተደርሶበታል እንዲሁም መዝገቦች ያለ ፍቃድ ታይተዋል ብሎ ለማመን የሚያበቃው በቂ ምክንያት አለው።

በምርመራችን የእርስዎ ጥንቃቄ የሚፈልግ መረጃ ላይ ጉዳት ደርሶበታል ብለን የምንደመድም ከሆነ፣ DOL ይህን ያሳውቅዎታል። በአሁኑ ወቅት፣ ወደ 650,000 የሚደርሱ ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለን እንገምታለን።

በተጨማሪም፣ ምርመራችን በየትኛውም ሌሎች እንደ የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፍቃድ መስጫ ስርዓት (DRIVES) የመሳሰሉ የ DOL ስርዓቶች ላይ ተጥሰው ሊሆኑ የሚችሉ የሚለውን እንድናስወግድ ረድቶናል። ይህን ያክል ካልን፣ አሁን በስርዓቶቻችን ላይ እጅግ በጥንቃቄ ቁጥጥር እያደረግን ነው።

DOL የሚሰበስበው ምን አይነት የሙያ ፍቃድ መስጫ መረጃዎች (ውሂብ) ናቸው?

የሙያ እና ንግድ ሥራ ፍቃድ መስጫ ስርዓት የፍቃድ ባለቤቶችን እና አመልካቾችን የተመለከቱ መረጃዎችን ያስቀምጣል። መረጃዎች ለተለያዩ የፍቃድ አይነቶች የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ። ከመረጃ ምድቦች መካከል ጥቂቶቹ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥሮች፣ የትውልድ ቀን፣ የመንጃ ፍቃድ ቁጥሮች፣ እና ሌሎች ማንነትን ለይተው የሚያሳውቁ መረጃዎች ናቸው።

የተደረሰበት መረጃ ምን ነበር?

ምንም እንኳን በስርዓታችን ላይ የሚያዙ ልዩ የመረጃ አይነቶች በሚይዙት የፍቃድ አይነት ላይ ተመስርተው ከግለሰብ ግለሰብ የሚለያዩ ቢሆንም መዝገቦቻችን እንደ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥሮች፣ የመንጅ ፍቃድ ቁጥሮች የመሳሰሉ ጥንቃቄ የሚፈልጉ መረጃዎችን ይይዛሉ። ለሁሉም ጥንቃቄ የሚፈልጉ መረጃዎቹ በሙያ እና ንግድ ሥራ ፍቃድ መስጫ ስርዓት ላይ ለተያዙ ሰዎች ማስታወቂያ እና እገዛ የምንሰጥ ቢሆንም መረጃዎቹ ተጋልጠው ሊሆን ይችላል። በስርዓታችን ላይ የሚያዙ ሰዎች በአገልግሎት ላይ ያለ ፍቃድ ያላቸው ግለሰቦችን፣ ፍቃዳቸው የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ፣ የታገደ እና የተዘረዘ ግለሰቦችን እንዲሁም ሌሎች ፍቃድ ለተሰጣቸው የንግድ ሥራዎች የግንኙነት ሠራተኛ ተብለው የተዘረዘሩ ግለሰቦችን ያጠቃልላሉ።

ለእኔ እና ለግል መረጃዬ/ውሂብ ጥበቃ ለማድረግ ምን እያደረጋችሁ ነው?

የእርስዎን ግላዊነትም ሆነ የግል መረጃዎን ደህንነት በጥብቅ እንቆጣጠራለን። በሙያ እና ንግድ ሥራ ፍቃድ መስጫ በስርዓታችን ላይ የሚካሄድ አጠራጣሪ ድርጊት መኖሩን እንዳወቅን ወዲያውኑ በስርዓታችንን በጊዜያዊነት እንዘጋዋለን። ቀጥለንም ተጽዕኖ ለሚፈጠርባቸው ሰዎች ማሳወቅ ከመጀመር በተጨማሪ፣ የክሬዲት ቁጥጥር ቅድሚያ እንሰጣቸዋለን እንዲሁም ከማንነት ስርቆት ጥበቃ እናደርግላቸዋለን።

የመረጃ ቴክኖሎጂ ሙያተኞቻችን የድህረገጹን አገልግሎት በድጋሚ ከመክፈታችን በፊት የስርዓቱን ደህንነት ለማረጋገጥ በመሥራት ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም፣ DOL ተጨማሪ የቴክኒክ ጥበቃዎች እና የስርዓት ቁጥጥር አቅሞችን በመተግበር ወደፊት እንደዚህ አይነት ክስተቶች የሚያጋጥሙበትን ሁኔታ ለመቀነስ እርምጃዎች እየወሰደ ነው።

አሁን ስጋት ካደረብኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?

በምርመራችን ጥንቃቄ የሚፈልጉ መረጃዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚደርስበት ከሆነ፣ ይህን የምናሳውቅዎ ከመሆኑም በተጨማሪ በዚህ ወቅት ተጨማሪ መረጃ እና እገዛ እናደርግልዎታለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በ DOL የተሰጠ የሙያ ፍቃድ ካሉዎት እና ጥንቃቄ ስለሚፈልግ መረጃዎ ስጋት ከገባዎ፣ ማንኛውም ግለሰብ ሊወስዳቸው የሚችላቸው ጥቂት ፈጣን እርምጃዎች እነሆ፡

  • ጠንቃቃ ሆኖ መቀጠል – የመለያ መግለጫዎችዎን እና የነጻ የክሬዲት ሪፖርቶችዎን በመመርመር ጠንቃቃ ሆነው እንዲቀጥሉ እናበረታታዎታለን።
  • በክሬዲት ፋይልዎ ላይ የመጭበርበር ማስጠንቀቂያ ወይም የደህንነት ማቆሚያ ሥራ ላይ ማዋል – የክሬዲት ቢሮዎች የመጭበርበር ማስጠንቀቂያዎች እና የደህንነት ማቆሚያዎችን ጨምሮ የክሬዲት ደህንነትዎን ለመጠበቅ መጠቀም የሚችሏቸው መሳሪያዎች አሏቸው።
  • የሚጠረጠር ድርጊትን ሪፖርት ማድረግ – የማጭበርበር ወይም የማንነት ስርቆት ተጎጂ ሆኛለሁ ብለው ካመኑ የፖሊስ ሪፖርት ያስመዝግቡ እንዲሁም ለአበዳሪዎችዎ እና ለሌሎች መዝገብዎችዎን ለማጽዳት የወንጀል ማስረጃ ለሚፈልጉ አካላት ለማስገባት የሪፖርቱን ኮፒ ይውሰዱ። ሪፖርቱ በተጨማሪም የማንነት ስርቆት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚቀርቡ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ሊያስችልዎ ይችላል።

ማግኘት የምችላቸው ተጨማሪ የድጋፍ ምንጮች ምንድን ናቸው?

የክሬዲት/ብድር ደህንነትዎን ለመጠበቅ ማግኘት የሚችሏቸው የድጋፍ ምንጮች የ Washington ግዛት የዋና ዓቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤትን (Washington State Office of the Attorney General) በ https://www.atg.wa.gov/credit-reports እና የፌደራል የንግድ ኮሚሽንን (Federal Trade Commission) በ https://www.consumer.ftc.gov/features/feature-0014-identity-theft ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት (Internal Revenue Service) የግብር መዝገቦችዎን ከመጭበርበር መጠበቂያ ዘዴ ያቀርብልዎታል።

ውሂብዎ አደጋ ላይ መሆኑን የሚያመለክት ከእኛ የተሰጠ ማስታወቂያ የሚደርስዎ ከሆነ፣ እንዴት ነጻ የክሬዲት መቆጣጠሪያን እንደሚያነቁ የተመለከቱ መመሪያዎች ይደርሱዎታል።

የሙያ እና የንግድ ሥራ ፍቃድ መስጫ ስርዓትን በተመለከተ ምን እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?

በጃኑዋሪ 24 ፣ 2022 ምርመራ በምናካሂድበት ወቅት የሙያ እና የሥራ ፍቃዶችን ለወሰዱ ሰዎች ጥበቃ ለማድረግ የሙያ ፍቃድ መስጫ ስርአታችንን በጊዜያዊነት ዘግተነው ነበር። DOL የመረጃቸውን ደህንነት ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለሙያ እና የሥራ ፍቃድ ብለቤቶች አገልግሎት መስጠቱን መቀጠል በሚያስችለው መልኩ የስርዓቱን ደህንነት ለማረጋገጥ እየሠራን ነው።

የሙያ እና ንግድ ፍቃድ መስጫ ድህረ ገጽ በተዘጋበት ወቅት የፍቃዴ የአገልግሎት ጊዜ ቢያበቃ ምን ማድረግ እችላለሁ?

DOL በዚህ ስርዓቱ በተዘጋበት ጊዜ ውስጥ ማንንም ሰው ፍቃዱን ባለማደሱ ምክንያት በገንዘብ ቅጣት፣ ቅጣት ወይም እቀባ አያደርግም። DOL ማብቂያ ቀናቸው ላይ ተመስርቶ ለፍቃድ እድሳቶች በአገልግሎት ቅድሚያ ይሰጣል።

Chatbot icon